Tuesday 19 October 2010

ሽምግልና


SHIMGLINA -

Thursday 14 October 2010

ገለልተኛ


GELELETEGNA -

Saturday 9 October 2010

“በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ”

በዛብህ በላቸው።

አባቶች፣ በክፉ ነገር ላይ ክፉ ነገር ሲያዩ “የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይላሉ”። በወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ላይ፣ ወያኔ ያወጣውን መግለጫ፣ እንደዚሁ ነው። እንደገና መዘርዘር የሚያስፈልግ ባይሆንም፣ በቆራጥ ታጋይነት ከትግል ባልደረቦቿ ጋር ስትታገል አደገኛ ተቃዋሚ ሁና በመገኘቷ፣ እዝብን በአደባባይ የጨፈጨፉት ወንጀለኞች በአገር ክህደት ሳይቀር ከሰዋት፣ በቃሊቲ ወህኒ ቤት ተሰቃይታ በምሕረት ሽፋን፣ ከሌሎች ጋር እንደወጣች ይታወቃል። የተለቀቀችበትንም ምክኒያት በሕዝብ ስብሰባ ተጠይቃ ስታብራራ፣ በምሕረት መወጣቷን አምና ግን ሽማግሌዎች ባቀረቡት ሰነድ ላይ መፈረሟን ብቻ አረጋገጠች። ይኽ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ፣ በሕግ የተሰጣት ምሕረት በማንአለብኝነት ተሽሮ፣ ለሁለት ዓመታት ያህል፣ ተሰቃየች። ከአቅሟ በላይ ጨከኑባት፣ አደቀቁአት።
ተሰቃየች ሲባል በተለመደ አነጋገር አይደለም። ያየችው የቁም ስቃይ ነው። ከሕጻን ልጇ፣ ከደካማና ባልቴት ወላጅ እናቷ፣ ከቤተሰብ፣ ከወዳጅና በተለይም አምናበት በቆራጥነት ከምትመራው ድርጅቷ ነው የተለየችው። የታሰረችው እንደሰብዓዊ ፍጡር አይደለም። ብቻዋን በጠባብና ጨለማ ክፍል ያለጠያቂና አነጋጋሪ ነው። በእስር እንዴት እንደቆየች ከሷ በስተቀር ሊገልጸው የሚችል ፍጡር አይኖርም። ቢቢሲ ሲጠይቃት ግን፣ በአንድ አጠቃላይ ቃል፣ “horrible” – “አሰቃቂ” ነበር ብላለች። ሊገለጽ የማይቻል ማለት ነው።
ምናልባት፣ የነበረችበትን የእስር ቤት ሁኔታ፣ ታላቁ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በዘረኛው መንግሥት በተመሳሳይ እስራት፣ ያሳለፉት ስቃይ በመጠኑ ሊገልጸው ይችል ይሆናል።
“For the next few weeks I was completely and utterly isolated. I did not see the face or hear the voice of another prisoner. I was locked up for 23 hours a day, with 30 minutes of exercise in the morning again in the afternoon. I had never been in isolation before, and every hour seemed like a year. There was no natural light in cell; a single bulb burned overhead 24 hours a day. I did not have a wrist watch and often thought it was the middle of the night when it was only late afternoon. I had nothing to read, nothing to write on or with, and no one to talk to. The mind begins to turn on itself, and one desperately wants something outside oneself on which to fix one’s attention. I have known men who took half a dozen lashes in preference to being locked up alone. After a time in solitary, I relished the company even of insects in my cell, and found myself on the verge of initiating conversations with a cockroach.” (Long Way to Freedom, Nelsen Mandela, pp 36-39, 1994)
“ለሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ፣ በይፋ ብቸኛ ሁኜ ነበር። የሌላ ሰው ፊት አላየሁም፣ ድምጽም አልሰማሁም። በቀን ለ23 ሰዓታት ይዘጉብኝ ነበር። ከጠዋቱና ከሰዓት በኋላ የግማሽ ሰዓት እንቅሰቃሴ በስተቀር። ከዚያ በፊት ብቸኛ ሁኜ አላውቅም። በመሆኑም እያንዳንዱ ሰዓት እንደ ዓመት ሆነብኝ። በታሰርኹበት የጠፈጥሮ ብርሀን አይታይም። አንዲት አምፑል ብቻ ለ24 ሰዓት ትነድ ነበር። የእጅ ሰዓት አልነበረኝም። ታዲያ ዘወትር ገና ከሰዓት በኋላ ሲሆን እኩለ ሌሊት ይምስለኝ ነበር። የማነበው የምጽፍበትም ሆነ የማወራው ሰው በፍጹም አልነበረኝም። አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ከራሱ ውጭ ሕሊናውን የሚያሳርፍበት ያስፈልገዋል። ያለዚያ አዕምሮ በጭንቀት በራሱ ውስጥ ይባዝናል። በዝግ ቤት ከመታሰር ይልቅ፣ ግማሽ ደርዘን ጅራፍ ተገርፈው የመረጡ ሰዎችን አውቃለሁ። በብቸኝነት ከቆየሁ በኋላ፣ በጎርኖዬ ካሉት ተባዮች ጋር ሳይቀር ቢጨንቀኝ መወዳጀት ግድ ሆነብኝ። ከቦረሮዎች ጋር ውይይትን ለመፍጠር ተቃረብኩ።”
ብለዋል። እነ መለስ ይኸን የመሰለውን ማሰቃየት የተማሩት ከዚህ የአፓርታይድ እና የኮሙዩኒስት ሥርዓት ነው። የወይዘሪት ብርቱካን እሥራት ግን፣ ከዚህም ይከፋል። በጣም ከባድ ነው። ወንጀሏ የተፈጸመው ዴሞክራሲያዊ ነኝ በሚል መንግስትና ኢትዮጵያውያን ነን በሚሉ አረመኔዎች በውሀ ቀጠነ የተፈጠረ ጭካኔ ነው። እንደነ ኒልሰን ማንዴላ የትግል ልምድ የላትም። በዚያ ላይ የጨቅላ ልጅ እናት ናት። በጾታዋም በዚህ ዓይነት ቆራጥ ትግል ከታዩት ጥቂት ሴቶች አንዷ ስትሆን በከተማ ውስጥ የተገኘች ታጋይ ናት። ሆኖም የነመለስ ግፍ የወለዳት ብርቱ ጅግና ናት።
ታዲያ ይኽ ሁሉ መሆኑ እየታውቀ፣ በውስጥም በውጪም ለሰብዓዊነት ክብር የሚጨነቁ ሁሉ ያለማሰለስ እይጮኹና እየተማጠኑ፣ ያንን ያህል ጊዜ ካሰቃዩአት በኋላ፣ ይቅርታ ጠይቀው መፍታት ሲገባቸው፣ እንደለመዱት በቱኪ ሽማግሌዎች ሽፋን መሰሪ መላቸውን መልለው፣ አማልለውና አባብለው ፈቱአት። ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን በእስራት ከተሰቃየችው በበለጠ ጊዜና ቃላት መርጠው ቅስሟን በመስበር የታጋይነቷንና ጥናቷን ለማኮላሸት ያስተላለፉት መግለጫ ነው። ይኸም እራሱን የቻለ የሕሊና ስቃይ ነው።
አሁንም እንኳ ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ስድስት በመቶ (99.6%) አሸነፍን ብለው ብርቱካንን አላመኑአትም። ስሟ ያስፈራቸዋል። በተለይ በሷ ምክኒያት ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ለጋሽ አገሮች ጋር ስለተፋጠጡና ቢያንስ ብርቱካን ካልተፈታች ዕውቅና እንደሚነሱአቸው ስለነገሩአቸው፣ ሽማግሌዎች ተብዬዎቹን ከጉድ አውጡን በማለት፣ መለስ፣ በተለመደ ሸሩ እንዲሳካለት አደረገ። በዕንቅርት ላይ ጆሮ ድግፍ ማለት ይኸ ነው።የዚያ ሁሉ ስቃይ ደረሰኝ፣ ዋሽተሽ ውጪ ሆነ። ምን ምርጫ አላት? ለማንስ አቤት ትበል?
ብርቱካን በዚህ ሁሉ ኢሰብአዊ ሥቃይ ውስጥ፣ “በይ” የተባለችውን እንድtል ብትገደድ ማን ሊተቻት ይችላል። በግል ድርሻዋ ለመከረኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካሁን ያደረገችው ብቻ ይበቃታል። ይኸ የውሸት መንግሥት ግን፣ ትውልዱን በውሸት ባህል ማበላሸቱ ያሳዝናል። በዚህች ወጣት ሴት ቦታ ሁኖ የደረሰውን ፈተና ለሚመለከት በጣም ከባድ ነው። አራሲቱን ነብር ድመት ሊያደርጓት ተረባርበዋል። እየሱስ እንኳ አምላክነት ሲኖረው “አቤቱ አቤቱ ለምን ትተወኛለህ?” ብሏል። ብርቱካንም የምትመራውን ሕዝብ ለምን ተዋችሁኝ ብትል እና ብትታዘብ ማን ይፈርድባታል። ሕዝቡ በተናጠል ሳይሆን በአንድነት “ሆ” ብሎ ሕዝባዊ ኃይሉን አላሳየም። ወደፊትም ቢሆን፣ ሌላ መፍትሔ ሊኖር አይችልም።
በመሠረቱ፣ ታላቁን ታጋይ ኔልሰን ማንዴላን እንዲፈቱ ግዴታ ለማስገባት በጠየቁአቸው ጊዜ “Prisoners cannot enter into contracts.” – “እስረኞች መዋዋል አይችሉም” እንዳሉት ወይዘሪት ብርቱካንም ይኸን ሁሉ ወያኔያዊ ስቃይ ውስጥ ሁና የፈረምችውም ሆነ የተናገረችው ቢኖር ሕጋዊነት የለውም። ሁሉንም ታሪክ ይፋረዳል። “ብሆር ለልጇ ስትል ተውጋች” ነውና”። በብርቱካን መፈታት ደስ ቢለንም አሁንም ስሟንና ወኔዋን ለመግደል፣ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያሉት ጥቃት ተሰምቶን አንድነታችንን እናጠንክር። እነዚህን መልቲዎች ጊዜ ሳንሰጥ እናሽቀንጥር።
ብርቱካን ምንጊዜም ጀግናችን ናት! እናከብራታለን።

Saturday 2 October 2010

SAMUNA


SAMUNA -